-->

Login or Register

Polls

Do you have a new millennium resolution for year 2000?
 

ምከር ቤቱ በሚሊኒየሙ በኢትዮጵያ ያለውን የሃይማኖት አንድነትና መቻቻል በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል እየተንቀሳቀሰ ነው

አዲስ አበባ ነሐሴ 21 ቀን 1999 - በሚሊኒየሙ በኢትዮጵያ ያለውን የሃይማኖት አንድነትና መቻቻል በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልና ሀገሪቱን ለአለም ተምሳሌት እንድትሆን የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምከር ቤት አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ በሃይማኖት አንድነትና መቻቻል ላይ በቀጥታ ህብረተሰቡን ለሚያስትምሩ የእምነት አባቶችና መምህራን ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ዛሬ በተጀመረው በዚሁ ስልጠና ላይ የምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ሐጂ መሐመድ አወል ኢትዮጵያ የተለያዩ ታሪክና ባህል ያላትና በርካታ ብሔር ብሔረሰብ የሚገኘባት አገር መሆኗን በዚህ እሴት ውስጥ የምትገኘውንና ተቻችሎ የመኖር ልምድ ያላትን ሃገር ለሌላው አለም ለማሰተዋወቅ ወጣቱ ትውልድ ሰለሃገሩ ታሪክና ባህል በቂ እውቀት ሊያኝ እንደሚገባ አስምረዉበታል፡፡

ምክር ቤቱም ለዚህ ስኬት ከህበረተሰቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው መምህራንና የሃይማኖት አባቶች ጋር በጋራ የሚሰራበትን ሁኔታ አመቻችቷል ብለዋል፡፡

የዛሬው ስልጠና ዋና ዓላማም የሃይማኖት አባቶች በሚሌኒየሙ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ አግኘተው ለህበረተሰቡ እንዲያስተምሩ ማድረግ ነው፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በኢትዮጵያ የኢራን እስላማዊ ኤምባሲ አንደኛ ጸሃፊ ሚስተር ሰይድ ቶፊቅ እንደገለጹት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀገሪቱ ያለውን አንድነትና መቻቻል ለማጠናከር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ይደግፋሉ፡፡

ለሶስት ቀናት በተዘጋጀውና የኢራን ኤምባሲ ከአባድር ትምህርት ቤቶች አስተዳደርና ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጋር በተዘጋጀው በዚሁ ስልጠና የሃይማኖት አባቶችና መምህራን ተገኘተዋል፡፡